በዋልያዎቹ ሽንፈት ያስተናገዱት አሠልጣኝ ከጋዜጠኞች ጋር ለፀብ ተጋበዙ

በዋልያዎቹ ሽንፈት ያስተናገዱት አሠልጣኝ ከጋዜጠኞች ጋር ለፀብ ተጋበዙ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳቸው የተረቱት የሞዛምቢክ አሰልጣኝ ቺኩንሆ ኮንዴ ከጨዋታው በኋላ ከተሰጠ የድህረ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ በኋላ ከጋዜጠኛ ጋር ለፀብ ሲጋበዙ ታይቷል።

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 3ኛ ጨዋታ በሜዳቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን አስተናግደው አንድ ለምንም የተረቱት ሞዛምቢኮች በጨዋታው ቡድናቸው ባሳየው እንቅስቃሴ እንዲሁም በተመዘገው ውጤት ደስተኛ አለመሆናቸውን በተለያየ መንገድ በተለይ በበይነ መረብ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ እየገለፁ ይገኛሉ።

ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የድህረ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ ቆይታ ያደረጉት የባለሜዳው ሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ቺኩንሆ ኮንዴ በቆይታቸው በስፍራው ከተገኙ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን አባላት ጋር የቃላት ምልልስ እንዲሁም ክርክር ሲገጥሙ አስተውለናል።

መግለጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ከአዳራሹ እየወጡ ከአንድ ጋዜጠኛ ጋር መደበኛ ባልሆነ መንገድ ክርክር የገጠሙት አሠልጣኝ ቺኩንሆ ኮንዴ ከጋዜጠኛው ጋር የጀመሩት ንትርክ ወደ ፀብ አምርቶ በገላጋዮች ታጅበው ከአዳራሹ እንዲወጡ ሆኗል።

በጉዳዩ ዙሪያ የሚኖሩ አዳዲስ ነገሮች ካሉ የምንመለስ ይሆናል።