በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የቅጣት ውሳኔ ላይ አዲስ ነገር ተሰምቷል

በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የቅጣት ውሳኔ ላይ አዲስ ነገር ተሰምቷል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የወላይታ ድቻ የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ አስተላለፈ

ጥቅምት 13 ወላይታ ድቻ እና ባህርዳር ከተማ ባደረጉት የሦስተኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ በታየው የስነ ምግባር ግድፈት ምክንያት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ላይ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። ከቅጣት ውሳኔው በኋላ ክለባቸው ወላይታ ድቻ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔው በድጋሚ እንዲታይ የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ኮሚቴውም ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔዎችን አሳርፏል።

በዚህ መሰረት አሰልጣኙ በዕለቱ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳደባቸው በሚል በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ የተላለፈባቸው የስድስት ጨዋታዎች እና የአምስት ሺሕ ብር ቅጣት የፀና ሲሆን በዕለቱ አራተኛ ዳኛውን ለመምታት መጋበዛቸው፣ የፀብ አጫሪነት ባህሪ ማሳየታቸው እና ጨዋታውን ለሦስት ደቂቃዎች እንዲዘገይ በማድረጋቸው የተወሰነው የአራት ጨዋታዎች እና የአምስት ሺሕ ብር ቅጣት ግን ቅጣቱ ተመሳሳይ ሆኖ ሳለ ሁለት የተለያየ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉ የሕግ ጥሰት ነው በሚል ውሳኔው እንዲሻር ተወስኗል።