FT | ኢት. ን. ባንክ | 0-0 | መከላከያ |
ጨዋታው ግብ ሳይቆጠርበት 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
90+3′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ቢንያም በላይ ወጥቶ ኤፍሬም ካሳ ገብቷል።
90′ ተጨማሪ ሰዐት – 4 ደቂቃ
84′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሳሙኤል ዮሐንስ ወጥቶ አምሀ በለጠ ገብቷል።
81′ የተሻ ግዛው ከሳሙኤል ታዬ ጋር በጥሩ ቅብብል ከተጫወተ በኃላ የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።
77′ የተሻ ግዛው ያመቻቸለትን ኳስ ሳሙኤል ታዬ ሞክሮ ወደውጪ ወጥቶበታል።
75′ የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
ማራኪ ወርቁ ወጥቶ የተሻ ግዛው ገብቷል።
67′ ቢንያም በላይ ከቀኝ መስመር ይዞ የገባውን ኳስ ሞክሮ አቤል መልሶበታል።
65′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ዳኛቸው በቀለ ወጥቶ ጌቱ ረፌራ ገብቷል።
62′ ታዲዮስ ወልዴ ከርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ አቤል ማሞ ይዞበታል።
60′ ሳሙኤል ዮሐንስ ከሳጥኑ ውስጥ የመታውን ኳስ ሳሙኤል ታዬ ተደርቦ አውጥቶታል።
56′ ማራኪ ወርቁ ከሳሙኤል ታዬ ጋር በአንድ ሁለት ቅብብል ተጫውቶ ገብቶ የመታውን ኳስ ፌቮ መልሶታል።
50′ ካርሎስ ዳምጠው ከ25 ሜትር ርቀት ላይ የመታውን ቅጣት ምት የንግድ ባንክ ተጫዋቾች ተደርበው አውጥተውታል።
46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።
የመጀመሪያው አጋማሽ ያለግብ አቻ ተጠናቋል።
45′ ተጨማሪ ሰዐት – 1 ደቂቃ
43′ ቴዎድሮስ በቀለ በጥሩ ሁኔታ ያሻገረውን ኳስ ማራኪ ወርቁ ከቅርብ ርቀት አግኝቶ ቢሞክርም ፌቮ አውጥቶታል።
37′ አዲሱ ተስፋዬ በሳሙኤል ዮሐንስ ላይ በሰራው ጥፋት ምክኒያት ቢጫ ካርድ አይቷል።
36′ ቢንያም በላይ በመልሶ ማጥቃት ይዞት የመጣው ኳስ ለታዲዮስ ወልዴ ደርሶት የመታውን ኳስ አቤል መልሶበታል።
31′ ዮናስ ገረመው ከርቀት ወደግብ የሞከረውን ኳስ አበል ማሞ እንደምንም ብሎ አውጥቶታል።
30′ ዳኛቸው ወርቁ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ግብ ከመሆን አድኖታል።
25′ የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
ምንይሉ ወንድሙ በጉዳት ተቀይሮ ወጥቶ ካርሎስ ዳምጠው ገብቷል።
18′ ቢንያም በላይ በግንባር የሞከረው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል።
16′ ምንይሉ ወንድሙ በደረሰበት ጉዳት ምክኒያት ከሜዳ ወጥቶ ህክምና ከተደረገለት በኃላ ተመልሶ ጨዋታውን ተቀላቅሏል።
10′ ሳሙኤል ሳሊሶ ከማራኪ ወርቁ የተቀበለውን ኳስ ሞክሮ በግብ ጠባቂው ፌቮ ድንቅ ጥረት ግብ ከመሆን ተርፏል።
5′ ሁለቱም ቡድኖች እስካሁን ምንም የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም።
1′ ተጀመረ!
ጨዋታው በመከላከያ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
የመጀመሪያ አሰላለፍ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1 – ኢማኑኤል ፌቮ
12 አቤል አበበ – 16 ቢኒያም ሲራጅ – 5 ቶክ ጀምስ – 7 ዳንኤል አድሃኖም
17 ሳሙኤል ዮሐንስ – 15 አዲሱ ሰይፋ – 88 ታዲዮስ ወልዴ – 21 ዮናስ ገረመው – 80 ቢኒያም በላይ
10 ዳኛቸው በቀለ
የመጀመሪያ አሰላለፍ – መከላከያ
1 አቤል ማሞ
3 ቴዎድሮስ በቀለ — 16 አዲሱ ተስፋዬ — 17 ምንተስኖት ከበደ — 2 ሽመልስ ተገኝ
19 ሳሙኤል ታዬ — 21 በሀይሉ ግርማ — 13 ሚካኤል ደስታ — 9 ሳሙኤል ሳሊሶ
7 ማራኪ ወርቁ — 14 ምንይሉ ወንድሙ