FTኢትዮ ኤሌክትሪክ 0-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ
53′ አዳነ ግርማ
ተጠናቀቀ !!
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 አሸፊነት ተጠናቋል።
90+3′ አብዱልከሪም ንኪማ እና ተስፋዬ መላኩ በፈጠሩት እሰጥ እገባ በቀጥታ ቀይ ካርድ ተሰናብተዋል።
ተጨማሪ ደቂቃ – 4
ቢጫ ካርድ
84′ አሸናፊ ሽብሩ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።
82′ ናትናኤል ከርቀት የሞከረውን ኳስ ሱሌማን አውጥቶታል።
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
80′ አበባው ቡታቀ ወጥቶ መሃሪ መና ገብቷል።
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
74′ አስቻለው ታመነ ወጥቶ ደጉ ደበበ ገብቷል።
የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
70′ ብሩክ አየለ ወጥቶ በሃይሉ ተተሻገር ገብቷል።
78′ ሳላዲን ሰኢድ የሞከረውን ኳስ ሱሌማን አድኖበታል።
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
66′ ያስር ሙገርዋ ወጥቶ ሳላዲን ሰኢድ ገብቷል።
የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
63′ ፍጹም ገብረማርያም ወጥቶ ሙሉአለም ጥላሁን ገብቷል።
60′ ራምኬል ከርቀት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል።
59′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ፎፋና ሞክሮ ምንተስኖት በድንቅ ሁኔታ ተደርቦ አውጥቶታል።
ጎልልል!!!ቅዱስ ጊዮርጊስ
53′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ አዳነ ግርማ ገጭቶ በሱሌማን እግሮች መሃል ሾልካ ግብ ሆናለች።
ቢጫ ካርድ!
52’አለምነህ ግርማ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።
ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።
እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሸ ያለ ግብ ተጠናቋል።
45′ ናትናኤል ከርቀተ የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወደ ውጪ ወጥቷል።
35’በሁለቱም በኩል ወደ ጎል ለመድረስ የሚደረገው ጥረት ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ በሚገኙ ተጫዋቾች ምክንያት ሊሳካ አልቻለም።
23′ ጨዋታው ፈጣን እንቅስቃሴ ቢታይበትም የግብ እድሎች እየተፈጠሩ አይደለም፡፡
9′ ከመስመር የተሻገረው ኳስ በግብ ጠባቂው ሲመለስ ራምኬል ሎክ አግኝቶ ቢሞክርም ቋሚውን ለትሞ ወጥቷል፡፡
8′ በስታድየም የተገኘው የተመልካች ቁጥር ከተጠበቀው በታች ነው፡፡
ተጀመረ!
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ አማካኝነት ተጀመረ፡፡
08:45 ሁለቱ ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
08:30 የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው እያሟሟቁ ይገኛሉ።
የኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰላለፍ
22 ሱሌይማን አቡ
11 አወት ገ/ሚካኤል – 21 በረከት ተሰማ – 15 ተስፋዬ መላኩ – 7 አለምነህ ግርማ
23 አሸናፊ ሽብሩ -10 ዳዊት እስጢፋኖስ – 24 ዋለልኝ ገብሬ – 9 ብሩክ አየለ
16 ፍፁም ገ/ማርያም – 4 ኢብራሂም ፎፋኖ
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
1 ፍሬው ጌታሁን
25 አንዳርጋለው ይላቅ -15 አስቻለው ታመነ 23 ምንተስኖት አዳነ – 4 አበባዉ ቡጣቆ
24 ያስር ሙገርዋ – 26 ናትናኤል ዘለቀ – 27 አብዱልከሪም ነኪማ
18 አቡበከር ሳኒ – 19 አዳነ ግርማ – 10 ራምኬል ሎክ