በ2025 የሚደረጉ የሴካፋ ውድድሮች ቀን እና ቦታ ተቆርጦላቸዋል

በ2025 የሚደረጉ የሴካፋ ውድድሮች ቀን እና ቦታ ተቆርጦላቸዋል

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር እንድታስተናግድ ስትመረጥ በሌላ ውድድር ላይ ደግሞ እንደማትሳተፍ ተረጋግጧል።

የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማህበር (ሴካፋ) የውድድር ዳይሬክተር የሆኑት የሱፍ ሞሲ የሴካፋ ውድድሮች ከቶታል ኢነርጂስ ካፍ የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ (ዋፍኮን) በፊት እንዲካሄዱ መወሰናቸው ታውቋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም “የእኛን ወኪሎቻችንን በመርዳት የዋፍኮን የተሻለ ዝግጅት እና ሌሎች ቡድኖች ደግሞ በዚህ ዓመት በጥቅምት ወር ለሚቀጥሉት WAFCON 2026 ማጣሪያ ይዘጋጃሉ” ሲሉ ተሰምተዋል።

በዚህም መሠረት

ቀደም ሲል አስተናጋጇ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ብሩንዲ እና ደቡብ ሱዳን ተሳታፊ መሆናቸውን ያረጋገጡበት እንዲሁም በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ደግሞ ተጨማሪ ቡድኖች ተሳታፊ መሆናቸውን እንደሚያረጋግጡ የሚጠበቁበት የሴካፋ ሲኒየር ሴቶች ቻምፒዮና ከሰኔ 5 እስከ 5 እንደሚካሄድ ሲታወቅ ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃም ኢትዮጵያ በውድድሩ እንደማትሳተፍ አረጋግጣለች።

ሴካፋ በዚህ አመት አመት የሚያዘጋጃቸው ሌሎች ውድድሮች ሲኖሩ ከእነዚህም ውስጥ (ከነሐሴ 28-መስከረም 9) የካፍ የሴቶች ክለብ ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ማጣሪያዎች በተመሳሳይ በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ሲደረጉ የአፍሪካ ከ17 አመት በታች የሴካፋ ማጣሪያ ውድድሮችን (ከሕዳር 6-21) ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደምታዘጋጅ ተረጋግጧል።