በአሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ የሚመራው ኢትዮጵያ መድን 3ለ0 በሆነ ውጤት ስሑል ሽረን በማሸነፍ ዓመቱን በድል እና በዋንጫ አድምቆ አጠናቋል።
ስሑል ሽረዎች ከድሬዳዋው ሽንፈት የስድስት ተጫዋቾችን መድኖች በበኩላቸው ከሀድያ ሆሳዕናው ድል ቅጣት ላይ ባስተናገደው በረከት ካሌብ ምትክ ረመዳን ሁሴንን በማስገባት ጀምረዋል።
የዓመቱ ምስጉን ዳኛ ዝርዝር ውስጥ ስማቸው በሰፈረው ዳንኤል ይታገሱ የተመራው የሊጉ የዓመቱ የማሳረጊያ መርሀ-ግብር መድኖች በይበልጥ ጫናዎችን ይጠቀሙ በነበሩት የንክኪ እንቅስቃሴያቸው በ11ኛው ደቂቃ ላይ መሪ መሆን የቻሉበትን ጎል አግኝተዋል። አቡበከር ሳኒ ከዳዊት ተፈራ ጋር ካደረጉት የአንድ ሁለት ቅብብል በኋላ ከአማካዩ በአግባቡ የደረሰውን ኳስ ወደ በመጀመሪያው የጨዋታው ሙከራ ጎልን አስመልክቶናል።
በበርካታ አዳዲስ ፊቶች የገቡት እና በተጋጣሚያቸውም በቀጣዮቹም ደቂቃዎች በተመሳሳይ በሽግግር አጨዋወት ጫና የበረከተባቸው ሽረዎች በ20ኛው ደቂቃ ከቅጣት ምት የግብ ዘቡ ዋልታ አንዶ ስህተት ታክሎበት ወገኔ ገዛኸኝ ለሻምፒዮኖቹ ሁለተኛ ጎልን አክሏል። ከሁለት ደቂቃዎች መልስ ደግሞ ዳዊት ከማዕዘን አሻምቶ ያሬድ በግንባር የገጫት ዋንጫ እና ዳዊት ከርቀት ካደረጓቸው ሙከራዎች ቀጥሎ በተወሰነ መልኩ መልሶ ማጥቃትን የተጠቀሙት ሽረዎች 41ኛው ደቂቃ ኬቨን አርጉዲ ሳጥን ውስጥ የሰጠውን ብሩክ ሀዱሽ ወደ ጎል መቶ አቡበከር ኑራ በጥሩ ቅልጥፍና ካዳናት ጠጣር ሙከራ በኋላ 45+3ኛው ደቂቃ ላይ ዳዊት ተፈራ ከማዕዘን ያሻማውን ዋንጫ ቱት በግንባር ገጭቶ ሦስተኛዋን ጎል አስቆጥሯል።
ከቆሙበት የጨዋታ ብልጫቸው ከዕረፍት መልስ ያስቀጠሉት መድኖች በ56ኛው ደቂቃ ወገኔ ገዛኸኝ ከጥሩ ቅብብል በኋላ ከሳጥኑ የግራ ክፍል የመታውን ኳስ በመጀመሪያው አጋማሽ ተቀይሮ የገባው የግብ ዘቡ ሙሴ ዕቋር አድኖበታል። እንደነበራቸው የሜዳ ላይ ብልጫ ከቆሙ ኳሶች ደጋግመው ያገኟቸውን ጥሩ ጥሩ አጋጣሚዎች መጠቀም ያልቻሉት መድኖች በእንቅስቃሴ መሻል ቢችሉም አጋማሹ ግን በሙከራዎች የደመቀ አልነበረም። አብዲሳ ጀማል እና መሐመድ አበራ እንዲሁም ከረጅም ደቂቃዎች በኋላ አብዲሳ በሙሴ ከተመለሰበት አጋጣሚ ውጪ ጨዋታው በመጨረሻም በኢትዮጵያ መድን 3ለ0 በሆነ አሸናፊነት ተጠናቋል።