ዐፄዎቹ ከአጥቂያቸው ጋር ተለያይተዋል

ዐፄዎቹ ከአጥቂያቸው ጋር ተለያይተዋል

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በፋሲል ከነማ ቤት ያሳለፈው ዩጋንዳዊው አጥቂ በስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱ ተሰምቷል።


በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ታድኖ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የኢትዮጵያን እግርኳስ የተዋወቀው ዩጋንዳዊው አጥቂ ማርቲን ኪዛ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አመርቂ እንቅስቃሴ በማሳየት በጥሩ ብቃት ጅማሮውን ቢያደርግም በጀመረው ልክ የውድድር ዓመቱን ማሳለፍ አልቻለም።

የቀድሞ የኬሲሲኤ፣ ቪላ፣ ኤክስፕረስ እና ቫይፐርስ አጥቂ የሆነው ኪዛ ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቶ የእግርኳስ ህይወቱን ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን ባሳለፍነው ክረምት ለሁለት ዓመታት በፋሲል ቤት ቆይታ ለማድረግ ፊርማውን አኑሮ የነበረ ቢሆንም በክለቡ ከአንድ ዓመት በላይ መቆየት አልቻለም። በዚህም በስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።