በርካታ ተጫዋቾቹን እያጣ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አንድ ተጫዋችን ወደ ስብስቡ አካቷል።
የፊታችን ሐምሌ 26 በአሜሪካ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያለበት እና እስከ አሁንም በድምሩ አስር የሚደርሱ ተጫዋቾችን እና ሁለት የአሰልጣኝ ቡድን አባሎቹን በቪዛ ምክንያት ከስብስቡ ውስጥ ለማጣት የተገደደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአንድ ተጫዋች ጥሪ ማድረጉን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
ከዚህ ቀደም ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የመጓዝ ዕድልን ያገኘው የሲዳማ ቡናው የመሐል ተከላካይ ጊት ጋትኩት ብሔራዊ ቡድኑን ዛሬ ተቀላቅሏል ቁመታሙ ተከላካይም ከቡድኑ ጋር በዛሬው ዕለት ኢምባሲ መግባት እንደቻለም ተሰምቷል።