ነብሮቹ አዲስ አሰልጣኝ ሾመዋል

ነብሮቹ አዲስ አሰልጣኝ ሾመዋል

ሀዲያ ሆሳዕናዎች ያለፈውን አንድ ዓመት ከቡድኑ ጋር ምክትል አሰልጣኝ በመሆን የሠሩትን አሰልጣኝ መሾማቸው እርግጥ ሆኗል።

የሀዲያ ሆሳዕና አመራሮች ያለፉት ሦስት ሳምንታት የአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ውል ማለቁን ተከትሎ በምትኩ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ሲያደርጉ የቆዩትን ጥረት በመጨረሻም ምክትል አሰልጣኝ በመሆን በቡድኑ ውስጥ ያለፉትን አንድ ዓመት ሲሠራ የቆየውን ወጣቱን አሰልጣኝ መሾማቸው ታውቋል።

ክለቡ እምነት ጥሎበት የሾመው አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድን ሲሆን ከነብሮቹ ጋር ያለፈውን አንድ ዓመት መቆየቱ ይታወሳል። ለአንድ ዓመት የፈረመው ወጣቱ አሰልጣኝ በቀጣዮቹ ቀናት ቡድኑን ለማጠናከር አብረውት የሚሠሩትን ረዳቶቹን በማሳወቅ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ በተጨዋችነት ዘመኑ በተለያዩ ክለቦች እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጫወት ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን ወደ አሰልጣኝነቱ በመግባት በኢትዮጵያ ቡና በምክትል እና በዋና እንዲሁም በዳሽን በማስከተል ወደ ከፍተኛ ሊግ በማምራት ያለፉትን ዓመታት በቡታጅራ ከተማ፣ ሀላባ ከተማ እና ወልዲያ ከተማ መስራታቸው ይታወቃል።