የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች አዲስ ክለብ ተቀላቅሏል።
በ2015 የውድድር ዓመት የሀገሩ ክለብ ካሬላ ዩናይትድን በመልቀቅ ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅሎ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ጋር በመተዋወቅ መድመቅ የቻለው ጋናዊው ባሲሩ ዑመር ከሦስት ዓመታት የኢትዮጵያ ቆይታ በኋላ ወደ ኢራቁ ክለብ ሞሱል አምርቷል።
በ2016 ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሊጉን ክብር ባነሳበት ዓመት የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን የተጎናፀፈው አማካዩ ከዚህ ቀደም በሀገሩ ክለቦች ‘ West African Football Academy (WAFA) ‘ ፣ አሻንቲ ኮቶኮ እና ካሬላ ዩናይትድ መጫወት የቻለ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለንግድ ባንክ በሃያ ስድስት ጨዋታዎች ተሳትፎ 2207’ ደቂቃዎች ቡድኑን ማገልገሉ ይታወሳል።