በካፒታል ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የአክሲዮን ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የቀጣይ ዓመት የክለቦች ክፍያ የገንዘብ መጠን ይፋ ተደርጓል።
የየሊጉ አክስዮን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤውን በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል እያካሄደ ይገኛል። በጉባኤው ላይ ከተያዙ ሁለት አጀንዳዎች መካከል አንዱ የሆነው የ2018 የክለቦች የክፍያ ዓመታዊ ጥቅል ምንያህል የገንዘብ መጠን እንዲሆን መወሰን ነበር።
በዚህ መሠረት ሶከር ኢትዮጵያ እንዳረጋገጠችው ከሆነ 70 ሚሊዮን ብር እንዲሆን መወሰኑን ሰምተናል።
በ2017 የውድድር ዘመን ተግባራዊ የተደረገ የክለቦችን የክፍያ ጣሪያ አመታዊ ጥቅል ክፍያም በዚሁ መሠረት 57,750,000(ሃምሳ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ሆኖ መፅደቁ ይታወሳል።
ዝርዝር ዘገባ ከቆይታ በኋላ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።