የሊጉ ተስተካካይ ጨዋታዎች ጥር 24 ይካሄዳሉ

 

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝመው የቆዩት የ3ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች በመጪው ጥር 24 ቀን 2007 ዓ.ም. እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በፕሮግራሙ መሰረት እሁድ ጥር 24 ቀን 2007 ዓ.ም ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቦዲቲ በማቅናት በ9 ሰአት ወላይታ ድቻን ሲገጥም ፤ ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከነማ ደደቢትን በተመሳሳይ 9 ሰአት ያስተናግዳል፡፡ በእኩል ነጥብ ከመሪዎቹ ተርታ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡና እና መብራት ኃይል ደግሞ በ10 ሰአት አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ይፋለማሉ፡፡

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር መርሃ ግብር ከ9ኛው ሳምንት በኋላ የቀን ለውጦች እንደመኖሩት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ከ10ኛ እስከ 13ኛ ሳምንት ያሉት ከፊል ጨዋታዎች በስራ ቀናት የሚደረጉ በመሆናቸው ወደ ሳምንቱ መጨረሻ ቀናት እንደሚሸጋሸጉ ፌዴሬሽኑ ጨምሮ ገልጧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *