የ2018 ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ከነሐሴ 25 ጀምሮ በአዲስ ፎርማት እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።
የ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ሲባል ከወትሮው በተለየ ቀደም ብሎ ከነሐሴ 25 ጀምሮ ሊካሄድ ቀን ቀን ተቆርጦለታል። አብዛኞቹ ክለቦች እስካሁን ምንም ዓይነት ዝግጅት ባይጀምሩም ከ19 ቀናት በኋላ የሚደረገው ውድድር ፎርማቱ ተቀይሮ ክለቦች በሚያስመዘግቡት ሜዳ በደርሶ መልስ መልኩ የሚከናወን እንደሚሆን ፌዴሬሽኑ ከደቂቃዎች በፊት አሳውቋል።
* ክለቦች የሜዳቸውን ጨዋታ የሚያደርጉበትን ሜዳ እስከ ነሐሴ 17/2017 ድረስ ማሳወቅ እንደሚገባቸውም ተነግሯል።