ብርቱካናማዎቹ ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ስብስባቸውን ቀላቅለዋል

ብርቱካናማዎቹ ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ስብስባቸውን ቀላቅለዋል

በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የሚመሩት ብርቱካናማዎቹ አማካይ አስፈርመዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ መሪነት በ48 ነጥብ 8ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት እና ቀደም ብለው ባለፉት ሁለት ዓመታት በአዳማ ከተማ ቆይታ ያደረገውን ተከላካዩ ሬድዋን ሸረፋን ያስፈረሙት ድሬዳዋ ከተማዎች አሁን ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት በስሑል ሽረ መለያ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገውን ጃዕፈር ሙደሲርን የግላቸው አድርገዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት በ 29 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2173′ ደቂቃዎች ስሑል ሽረን ያገለገለው ይህ የአማካይ ከዚህ ቀደም በስልጤ ወራቤ፣ ቤንጂማጂ ቡና እንዲሁም ለወጣት ብሄራዊ ቡድን መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የብርቱካናማዎቹ የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሁለተኛ ፈራሚ በመሆን ቡድኑን ተቀላቅሏል።