ብርቱካናማዎቹ የአማካይ ተጫዋቻቸውን ለተጨማሪ ዓመት በቡድናቸው ለማቆየት ተስማምተዋል።
በሁለት ቀናት ውስጥ ሬድዋን ሸረፍን እና ጃዕፋር ሙደሲርን በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የሚመሩት ድሬደዋ ከተማዎች አሁን ደግሞ የአማካይ አቤል አሰበን ውል ለማራዘም ተስማምተዋል።
የቡርትካናማዎቹ የታዳጊ ቡድን ፍሬ በመሆን ያለፉትን አምስት ዓመታት ቡድኑን ሲያገለግል የቆየው እና ከድሬደዋ ከተማ ማሊያ ውጭ ሌላ መለያ ለብሶ የማያቀው አቤል አሰበ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ቡድኑን ለማገልገል መስማማቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
ድሬደዋ ከተማ በቀጣዮቹ ቀናትም በተመሳሳይ ውላቸውን የጨረሱ የነባር ተጫዋቾችን የማቆየት እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል ወደ ዝውውሩ በስፋት እንደሚገቡ ሰምተናል።