ጦሩ አጥቂ አስፈረመ

ጦሩ አጥቂ አስፈረመ

ከሰሞኑን ወሳኝ ወሳኝ ዝውውሮችን እየፈፀሙ የሚገኙት መቻሎች ከመድን ጋር ለመቀጠል ተስማምቶ የነበረውን አጥቂ የግላቸው አድርገዋል።

በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ራሱን አጠናክሮ ለመቅረብ ከአሠልጣኝ ቅጥር ጀምሮ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ እየቀላቀለ የሚገኘው መቻል ከትናንት በስትያ ቸርነት ጉግሳን፣ የአብስራ ተስፋዬን እና ብሩክ ማርቆስን ማስፈረሙን እና የውብሸት ጭላሎን ውል ማራዘሙን ዘገባ አቅርበን ነበር። የዝግጅት ክፍላችን አሁን ባገኘችው መረጃ መሠረት ደግሞ ከቀናት በፊት በመድን ማሊያ ለመቆየት ስምምነት ላይ ደርሶ የነበረው አጥቂ መዳረሻው መቻል እንደሆነ ተሰምቷል።

የቀድሞ የሰበታ ከተማ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ለገጣፎ ለገዳዲ አጥቂ የነበረው መሐመድ አበራ ከዚህ ቀደም በመቻል ቤት ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ግልጋሎት ሰጥቶ የነበረ ሲሆን አሁን ዳግም ወደ ክለቡ መመለሱ ታውቋል።