በአዳዲስ ዝውውሮች ቡድኑን በማጠናከር የተጠመደው አዲስ አዳጊው ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
በዛሬው ዕለት የስድስት ተጫዋቾች ዝውውር ያጠናቀቁት ሸገር ከተማዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት አስራ ሦስተኛው ፈራሚያቸውን አግኝተዋል። ቡድኑን የተቀላቀለው ደግሞ ቀደም ብሎ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ውሉን ለማራዘም ተስማምቶ የነበረው ግብ ጠባቂው ያሬድ በቀለ ነው። ከሀድያ ሆሳዕና ክለብ አመራሮች ባገኘነው መረጃ መሰረት ተጫዋቹ ቀደም ብሎ ከነብሮቹ ጋር ውሉን ለማራዘም ተስማምቶ በአሳዳጊ ክለቡ ለመቆየት ከውሳኔ ላይ ደርሶ እንደነበር ጠቅሰን የነበረ ቢሆንም በስተመጨረሻ ግን መዳረሻውን ሸገር ከተማ በማድረግ ወደ አዲስ አዳጊው ክለብ አምርቷል።
በዚህ ዝውውር ዙርያ የሚፈጠሩ አዳዲስ ነገር ካሉም ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።