ፈረሰኞቹ የአጥቂያቸውን ውል አራዘሙ

ፈረሰኞቹ የአጥቂያቸውን ውል አራዘሙ

ዘግይተውም ቢሆን ወደ ዝውውሩ የገቡት ፈረሰኞቹ የነባር ተጫዋቻቸውን ውል አራዝመዋል።


በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚሰለጥኑት ፈረሰኞቹ ለከርሞ ቡድናቸውን ለማጠናከር ወደ ዝውውሩ ለመግባት ቢዘገዮም አሁን የአጥቂያቸውን ተገኑ ተሾመን በክለቡ የሚያቆየውን ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ ገብተዋል።

ከ2010 ጀምሮ ከአስራ ሰባት ዓመት በታች ውድድር ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን ለሰባት ዓመታት ቡድኑ ጋር አብሮ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ተገኑ ከፈረሰኞቹ ጋር ለሁለት ዓመት የሚቆይ መሆኑ ተረጋግጧል።