ብርቱካናማዎቹ  ቅድመ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበት ጊዜ ታውቋል

ብርቱካናማዎቹ ቅድመ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበት ጊዜ ታውቋል

ድሬዳዋ ከተማ ለ2018 የውድድር ዘመን ቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የሚያደርግበት ወቅት ታውቋል።

በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የሚመሩት ቡርትካናማዎቹ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በሊጉ ጅማሮ እንደነበራቸው ድንቅ አጀማመር ሳይሆኑ የኋላ የኋላ የውጤት ማሽቆልቆል አጋጥሟቸው በሊጉ በ48 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። ለከርሞ የቡድኑን ስብስብ ለማጠናር ወደ ዝውውሩ የገቡት ቡርትካናማዎቹ ሬዲዋን ሸሪፍ ፣ የአብስራ ሙልጌታ እና ጃዕፋር ሙደሲርን ማስፈረማቸው አይዘነጋም።

አሁን ቡድኑ ቀሪ የዝውውር ስራዎችን እየሰራ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ጊዜያቸው መቼ እንደሚጀመር ታውቋል። እንደዚህ ቀደሙ ከዓመት በኋላ ወደ በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተጉዘው ዝግጅታቸውን በሚቀጥለው ሳምንት የሚጀምሩ ሲሆን በድሬደዋ የሚዘጋጀውን ድሬ ሲቲ ካፕ ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።