ፈረሰኞቹ የአጥቂ መስመር ተጫዋች አስፈርመዋል

ፈረሰኞቹ የአጥቂ መስመር ተጫዋች አስፈርመዋል

ዛሬ ወደ ዝውውር ገበያው የገቡት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የመጀመሪያ ተጫዋቻቸውን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።


በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ፈረሰኞቹ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ቡድናቸውን ለማጠናከር ዘግይተውም ወደ ዝውውር ገበያው የገቡት ፈረሰኞቹ የአጥቂያቸውን ተገኑ ተሾመን ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ የገቡ ሲሆን አሁን ደግሞ አዲስ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

መነሻውን ከወደ ጋምቤላ ያደረገው ቡአይ ኩዌት በዚህ ዝውውር ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለ የመጀመሪያው ተጫዋች መሆን ችሏል። ያለፈውን የውድድር አመት በከፍተኛ ሊጉ እየተሳተፈ ለሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ያሳለፈ ሲሆን 8 ጎሎችን ማስቆጠር የቻለው ይህ የመስመር አጥቂ በፈረሰኞቹ ቤት ለሁለት አመት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል።