ወልዋሎ የዝውውር መስኮቱን የመጀመርያ ፈራሚ አግኝቷል።
አሰልጣኝ ግርማ ታደሰን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥረው ለ2018 የውድድር ዓመት ቡድናቸውን ለማጠናቀር በእንቅስቃሴ ላይ የቆዩት ቢጫዎቹ የክረምቱ የዝውውር መስኮት የመጀመርያ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል። ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ደግሞ ባለፉት የውድድር ዓመታት በባህር ዳር ከተማ ቆይታ ያደረገው አማካዩ ፍሬው ሰለሞን ሆኗል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በጣና ሞገዶቹ ቤት በሁሉም 34 የጨዋታ ሳምንታት ተሳትፎ 2682′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው አማካዩ የሕክምና ምርመራውን ካጠናቀቀ በኋላ ዛሬ በይፋ ቡድኑን ተቀላቅሏል። ፍሬው ሰለሞን (ጣቁሩ) ከዚህ ቀደም በሀላባ ከተማ፣ ሙገር ሲሚንቶ፣ መቻል፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና እንዲሁም ባህርዳር ከተማ መጫወቱ ይታወሳል።