ወልዋሎዎች ተከላካዩን ለማስፈረም ተስማምተዋል

ወልዋሎዎች ተከላካዩን ለማስፈረም ተስማምተዋል

ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ቆይታ ያደረገው ተጫዋች ወደ ወልዋሎ ለማምራት ተስማምቷል።

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ከሚገኙ ክለቦች መካከል የሚጠቀሱት ወልዋሎዎች ቡድናቸውን መጠናከር ተያይዘውታል። ቀደም ብለው ፍሬው ሰለሞን፣ በየነ ባንጃ እና ኢብራሂም መሐመድ ያስፈረሙት ቢጫዎቹ አሁን ደግሞ የመሃል ተከላካዩ ፍሬዘር ካሳን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

ፍሬዘር ካሳ ባለፉት ሁለት ዓመታት በባህር ዳር ከተማ የመከላከል ጥንካሬ ጉልህ ድርሻ ከተወጡ ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመትም በ28 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2431′ ደቂቃዎች ቡድኑን ማገልገል ችሏል። በቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ እና ዋናው ቡድን፣ ድሬደዋ ከተማ፣ ሃዲያ ሆሳዕና፣ ባህር ዳር ከተማ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ተከላካዩ አሁን ደግሞ የቢጫዎቹ አራተኛ ፈራሚ ለመሆን ከስምምነት ደርሷል።