ምኞት ደበበ በዐፄዎቹ ቤት ለመቆየት ተስማማ

ምኞት ደበበ በዐፄዎቹ ቤት ለመቆየት ተስማማ

ግዙፉ ተከላካይ ከፋሲል ከነማ ጋር ለመቆየት ተስማምቷል።

ቀደም ብለው ግብ ጠባቂውን ሞየስ ፖዎቲ እና ሁለገቡን ናትናኤል ገብረጊዮርጊስን ለማስፈረም የተስማሙት ፋሲል ከነማዎች አሁን ደግሞ ፊታቸውን የነባር ተጫዋቾች ውል ወደ ማራዘም በማዞር የግዙፉን ተከላካይ ምኞት ደበበን ውል ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም ተስማምተዋል።

ከዚህ ቀደም በደደቢት፣ አዳማ ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ባለፉት ሁለት ዓመታት በዐፄዎቹ ቤት የተጫወተው የመሐል ተከላካዩ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ32 ጨዋታዎች ተሳትፎ በ2880′ ደቂቃዎች ቡድኑን ማገልገሉ ሲታወስ አሁን ደግሞ ከክለቡ ጋር ያለውን ውል ማራዘሙን ተከትሎ በ2018 የውድድር ዓመት በዐፄዎቹ መለያ የምናየው ይሆናል።