ባለፈው የውድድር ዓመት ከስሑል ሽረ ጋር ቆይታ የነበረው አማካይ ወደ ወልዋሎ ለማምራት ተስማማ።
አሰልጣኝ ግርማ ታደሰን ቀጥረው ፍሬው ሰለሞን፣ በየነ ባንጃው፣ ኢብራሂም መሐመድ፣ ፍሬዘር ካሳ፣ ሰመረ ሃፍታይ፣ ጌትነት ተስፋዬን፣ ፍቃዱ መኮንን እና ነፃነት ገብረመድህንን ለማስፈረም ተስማምተው የኪሩቤል ወንድሙን ውል ያራዘሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ አማካዩ ሙሉዓለም መስፍንን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
ወደ ክለቡ ለማምራት ከስምምነት ከደረሰ በኋላ ባለፈው ሳምንት ዕሮብ የህክምና ምርመራውን በማከናወን ዛሬ ክለቡን ለመቀላቀል የተስማማው ይህ ተጫዋች ባለፈው የውድድር ዓመት ከስሑል ሽረ ጋር በነበረው ቆይታ በ 32 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2868′ ደቂቃዎች ቡድኑን አገልግሏል።
በአርባምንጭ ከተማ ከጀመረው የእግር ኳስ ህይወቱ በኋላ በሲዳማ ቡና ሁለት የውድድር ዓመታት ከዛ በመቀጠል በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫውቶ የፈረሰኞቹ የአራት ዓመት ቆይታው ካገባደደ በኋላም ወደ ቀድሞ ክለቡ ሲዳማ ቡና በማምራት ቆይታ አድርጎ ሁለት ዓመታት በወልቂጤ ከተማ በተጠናቀቀ የውድድር ዓመት ደግሞ በስሑል ሽረ ቆይታ ያደረገው አማካዩ በ2018 በቢጫው መለያ ለመጫወት ከስምምነት ደርሷል።