ዋልያዎቹ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ መቼ እንደሚካሄድ ታውቋል

ዋልያዎቹ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ መቼ እንደሚካሄድ ታውቋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታ የሚያደርግበት ከተማ እና ቀን ታውቋል።

ነሐሴ 30 እና ጳጉሜ 4 ቀን ከግብፅ እና ሴራሊዮን ጋር ለሚያደርጋቸው ሁለት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅት የጀመረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቅርቡ ከኢትዮጵያ መድን ጋር እና ወላይታ ድቻ ጋር ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጨዋታዎቹም የት እና መቼ እንደሚካሄዱ ግን አለመወሰኑን ገልፀን እንደታወቀ የምናሳውቃችሁ መሆኑን ዘግበን ነበር።

አሁን ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ሊደረግ የታሰበው ጨዋታ እንደተሳካ እና የፊታችን ሐሙስ ነሐሴ 22 ቀን በአዳማ ከተማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታውን ረፋድ አራት ሰዓት ላይ ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን አውቀናል።

በቀጣይ ቅዳሜ ነሐሴ 24 ቀን በድጋሚ ከእራሱ ከኢትዮጵያ መድን ጋር አልያም ከሌላ ቡድን ጋር ብሔራዊ ቡድኑ እንደሚጫወትም አውቀናል።