ባሳለፍነው የውድድር አመት የከፍተኛ ሊጉ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ መዳረሻው ፈረሰኞቹ ጋር ሆኗል።
አጥቂውን ቡአይ ኩዌት፣ አማካዩን አበባየሁ ዮሐንስ ፣ የመስመር ተከላካዩን መሳፍንት ጳውሎስን እና የመሃል ተከላካዩን ጥዑመልሳን ኃይለሚካኤልን በማስፈረም የተገኑ ተሾመን እና የአማካያቸውን አብርሃም ጌታቸውን ውል ያራዘሙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አሁን ደግሞ የአጥቂ አማካዩን አዲሱ አቶላን ወደ ክለባቸው ቀላቅለዋል።
በሲዳማ ቡና ና በመቻል እንዲሁም በሀዋሳ ከተማ መጫወት የቻለው ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ በሚሳተፈው በንብ ስፖርት ክለብ ተጫውቶ ያሳለፈውና በውድድር ዓመቱ 14 ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አግቢ በመሆን የጨርሰ ሲሆን በፈረሰኞቹ ቤት ለ2 ዓመት የሚያቆየውን ፊርማ አኑሯል ፡፡