የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ዋልያዎቹን የምትገጥመው ሴራሊዮን ስብስቧን ይፋ አደረገች።

ለ2026 የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ የተደለደሉት ሴራሊየኖች ከኢትዮጵያ እና ጊኒ ቢሳው ላሉባቸው ሁለት የዓለም ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች ቡድናቸውን ይፋ አደርገዋል። የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ መሐመድ ካሎን በሁለቱም የማጣርያ ጨዋታዎች የሚጠቀሟቸው 26 ተጫዋቾችን ዛሬ ይፋ ስያደርጉ በቡድኑም በውጪ እና በሀገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን አካተዋል።

ለዓመታት የብሄራዊ ቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ከሰሩ በኋላ ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት ተረክበው በመጀመርያው ከዋልያዎቹ ጋር ባደረጉት የማጣርያ ጨዋታ ቡድኑን ከመሩት የአርባ ዘጠኝ ዓመቱ አሰልጣኝ አሚዱ ካሪም የአሰልጣኝነት መንበሩን የተረከቡት አሰልጣኝ መሐመድ ካሎን በአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች ባገኙት ውጤት ደስተኛ እንደሆኑነ ሴራሊዮንን ለመወከል በተጠሩት ተጫዋቾች እንደሚተማመኑ በአፅንዖት ገልፀዋል።

ምድቡን ግብፅ በ16 ነጥብ ስትመራ ቡርኪናፋሶ በ11 ሁለተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ሴራልዮን ደግሞ በ 8 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ እና ጊኒ ቢሳዋ ደግሞ በእኩል ስድስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።