የአዲስ አበባ ስታዲየም ዳግም የሊጉ ውድድር ይደረግበት ይሆን?

የአዲስ አበባ ስታዲየም ዳግም የሊጉ ውድድር ይደረግበት ይሆን?

አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲየም ዳግም የሊጉ ጨዋታ ሊደርግበት ይችል ይሆን ስትል ሶከር ኢትዮጵያ አዲስ መረጃ አግኝታለች።


አሁጉራዊ እና የሀገር ውስጥ ውድድሮች መማስተናገድ ከቻለ የሰነባበተው አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲየም የወንዶች ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታን በእድሳት እና በሌሎች ምክንያት ማስተናገድ ካቆመ አፋት ዓመት አስቆጥሯል።

ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ ከሆነ የአዲስ አበባ ስታዲየም ዳግም ከዓመታት በኋላ የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታን እንዲስተናገድበት ለማድረግ የተደረገው ጥረት የተሳካ ይመስላል።

ዛሬ የእግርኳሱ የበላይ አካል ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የሊግ ካምፓኒው ፕሬዝደንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ እንዲሁም ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን እና አቶ ክፍሌ ሰይፉ የሊጉ አክስዮን ዋና ስራ አስኪያጅ በጋራ በመሆን የአዲስ አበባ ከተንቲባ ክብርት አዳነች አበቤ ጋር በፅህፈት ቤታቸው በመገኘት ውይይት አድርገው እንደነበረ ሰምተናል።

በውይይቱም መልካም ነገር እንደተገኘ እና አዲስ አበባ ስታዲየም ዳግም ውድድር እንደሚጀመርበት መልካም ተስፋ ተጥሎበት ስብሰባው እንደተቋጨ ጭምር ስምተናል።