ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለት አጥቂዎችን ከከፍተኛ ሊግ አግኝቷል

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለት አጥቂዎችን ከከፍተኛ ሊግ አግኝቷል

በዝውውሩ ላይ ብዙም ተሳትፎ እያደረገ የማይገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከከፍተኛ ሊግ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል።

በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚሰለጥነው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም እና አንድ አዲስ ፈራሚ ተጫዋችን በመያዝ ነገ በአዳማ ዝግጅቱን እንደሚጀምር ይጠበቃል። ዛሬ ደግሞ ከከፍተኛ ሊግ  ሁለት አጥቂዎችን ለማስፈረም ተስማምቷል። ተጫዋቾቹ ቤዛ መድኅን እና ሀሰን ሁሴን ናቸው።

የመጀመርያው ፈራሚ አጥቂ ቤዛ መድኅን ከዚህ ቀደም በሊጉ በወልቂጤ ከተማ ሲጫወት የሚታወቅ ሲሆን በከፍተኛ ሊግ ገላን ከተማ፣ ሀምበርቾ እና ዘንድሮ በነቀምቴ ከተማ ጥሩ ጊዜ እንዳሳለፈ ሲታወቅ አሁን መዳረሻው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሆኗል።

ሌላኘው ፈራሚ አጥቂ ሀሰን ሁሴን ሲሆን ሮቤ ከተማ ከአንደኛ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ወደ ከፍተኛ ሊግ ሲያድግ ትልቁን ሚና የተወጣው አጥቂ የውድድሩ ኮከብ ነበር። ያለፉትን ሦስት ዓመታት በቤንች ማጂ ቡና ጥሩ ቆይታ የነበረው አጥቂው አሁን ማረፊያው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሆኗል።