የግራ መስመር ተከላካዩ ወደ ቀድሞ ቤቱ ተመልሷል

የግራ መስመር ተከላካዩ ወደ ቀድሞ ቤቱ ተመልሷል

ያለፈውን አንድ ዓመት በጣና ሞገዶቹ ቤት የቆየው የግራ መስመር ተከላካይ ወደ ቀደመ ክለቡ ተመልሷል።

በቅርቡ ይፋዊ በሆነ መንገድ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በስምምነት የተለያዩት ዐፄዎቹ ዋና አሰልጣኛቸውን ዮሐንስ ሳህሌን መሾማቸው እርግጥ ሆኗል። በተጨማሪም የምኞት ደበበን ውል እንዳራዘሙት ሁሉ ግብ ጠባቂ ሞይስ ፓውቲ፣ የአብዱላዚዝ አማን፣ የናትናኤል ገብረጊዮርጊስ እና ያሬድ ብርሃኑን ዝውውር ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ የግራ መስመር ተከላካይ አምሳሉ ጥላሁን ዝውውር ማጠናቀቃቸው እርግጥ ሆኗል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በጣና ሞገዶቹ ቤት ቆይታ የነበረው አምሳሉ ጥላሁን ከታዳጊ ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ በዳሽን ቢራ በመቀጠል ለፋሲል ከነማ ለስምንት ዓመታት ቆይታ አድርጎ የነበረ ሲሆን ከአንድ ዓመት መለያየት በኋላ ዳግም ወደ እናት ክለቡ ለመመለስ መስማማቱን አውቀናል።