ሴኔጋላዊው የግብ ዘብ ከጣና ሞገዶቹ ጋር ለመቀጠል ተስማማ

ሴኔጋላዊው የግብ ዘብ ከጣና ሞገዶቹ ጋር ለመቀጠል ተስማማ

ባህር ዳር ከተማዎች የወሳኝ ተጫዋቻቸው ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።

በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመሩት የጣና ሞገዶች በዝውውር መስኮቱ ከዚህ ቀደም ዮሐንስ ደረጄ፣ ብሩክ ሰሙ፣ ማንያዘዋል ካሳ እና አናንያ ጌታቸውን በማስፈረም የመሳይ አገኘሁ፣ ፍቅረ ሚካኤል ዓለሙ፣ አምሳሉ ሳለ፣ ግርማ ዲሳሳ፣ ይገርማል መኳንንት እና ሄኖክ ይበልጣልን ዉል ማራዘማቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የሴኔጋላዊውን ግብ ጠባቂ ፔፔ ሴይዶ ውል ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ 30 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2700′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ቁመታሙ ግብ ጠባቂ በሀገሩ ክለቦች ኒያሪ ታሊ፣ ኤ ኤስ ሲ ጃራፍ እና በጀነሬሽን ፉት ከተጫወተ በኋላ በዴኒማርኩ ክለብ ጃመርባግት ቆይታ አድርጎ በሀድያ ሆሳዕና እና ባህር ዳር ከተማ ሁለት የውድድር ዓመታት መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ በጣና ሞገዶቹ ቤት ለመቆጠል ከስምምነት ደርሷል።