በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመቻል ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ሽረ ምድረ ገነት አምርቷል።
በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ካሉ ክለቦች አንዱ የሆነው በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመራው ሽረ ምድረ ገነት ቡድኑን ማጠናከሩን ቀጥሎበታል። ከቀናት በፊት የሽመክት ጉግሳን ዝውውር ያጠናቀቀው ክለቡ አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው ውድድር ዓመት በመቻል ቆይታ የነበረው አጥቂው ዳንኤል ዳርጌን አስፈርሟል።
በ2017 የውድድር ዓመት በ20 ጨዋታዎች ተሳትፎ
ያደረገው ወጣቱ ተጫዋች በ2016 ከአህመድ ሁሴን ጋር በጣምራ የከፍተኛ ሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በገላን ከተማ እና ኦሮሚያ ፖሊስ መጫወቱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ወደ ሽረ ምድረገነት ለማምራት ፊርማውን አኑሯል።