ደጉ ደበበ ምክትል አሰልጣኝ ሆኗል

ደጉ ደበበ ምክትል አሰልጣኝ ሆኗል

በኢትዮጵያ እግርኳስ ከፍ ያለ ስም ካላቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ደጉ ደበበ ምክትል አሰልጣኝ ሆኗል።

ከሃያ ዓመታት በላይ በወጥነት ከተለያዩ ስኬቶች ጋር በኢትዮጵያ እግርኳስ መድመቅ የቻለው እና እግር ኳስን ካቆመ በኋላ በአርባምንጭ ከተማ ቴክኒክ እና ቡድን መሪ በመሆን ያለፈውን አንድ ዓመት ያገለገለው ደጉ ደበበ የነብሮቹ ምክትል አሰልጣኝ መሆኑ ታውቋል።

ከሳምንታት በፊት የቀደሞ ተጫዋች እና በሀዲያ ሆሳዕና ለአንድ ዓመት ምክትል ሆነው የሰሩትን ካሊድ መሐመድን የሾመው ክለቡ አሁን ደግሞ ረዳት አሰልጣኙን ደጉ ደበበን ማድረጋቸው ታውቋል።

ደጉ ደበበ በአርባምንጭ ከተማም በኋላም በቅዱስ ጊዮርጊስ ረጅም ዓመት የተጫወተ ሲሆን በመቀጠል በወላይታ ድቻ ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል። ደጉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአንበልነት ለዓመታት ያገለገለ ሲሆን በርከት ያሉ በዋንጫ የታጀቡ ስኬቶች ያሉት ተጫዋች ነበር። አሁን የነብሮቹ ረዳት አሰልጣኝ መሆን ችሏል።