የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ2026 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ከታንዛኒያ ጋር ለሚያደርጋቸው የማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ለ31 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል።
ሉሲዎቹ ጥቅምት 12 እና 18 ለሚያደርጓቸው የ2026 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር ወሳኝ ጨዋታ ዝግጅት አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ከሀገር ውስጥ ክለቦች ለ31 ተጫዋቾች ጥሪ አስተላለፈዋል። በዚህም መሠረት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ ተጫዋቾች ማለትም
ግብ ጠባቂዎች
ታሪኳ በርገና (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ቤቴልሔም ዮሐንስ (መቻል)
አበባ አጄቦ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ሮማን አምባዬ (ሸገር ከተማ)
ተከላካዮች
ለምለም አስታጥቄ (ሀዋሳ ከተማ)
ታሪኳ ዴቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ቅድስት ዘለቀ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ትግስት አዳነ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ብርቄ አማረ (መቻል)
ድርሻዬ መንዛ (መቻል)
ሰናይት ሸጎ (መቻል)
እጸገነት ብዙነህ (መቻል)
ብዙዓየው ታደሰ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
አማካዮች
ዙፋን ደፈርሻ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
እመቤት አዲሱ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ጸጋ ንጉሤ (ሀዋሳ ከተማ)
እጸገነት ግርማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ገነት ኃይሉ (መቻል)
ስመኝ ምህረት (ሲዳማ ቡና)
ቤዛዊት ንጉሤ (መቻል)
ጋብሬላ አበበ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
ቤቴልሄም መንተሎ (መቻል)
መሳይ ተመስገን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
አጥቂዎች
እሙሽ ዳንኤል (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ሴናፍ ዋቁማ (መቻል)
ዳግማዊት ሰሎሞን (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
ንግስት በቀለ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ማህሌት ምትኩ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
ምርቃት ፈለቀ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ቤቴልሄም ታምሩ (ሸገር ከተማ)
ሰላማዊት ጎሳዬ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከነገ (ሐሙስ መስከረም 15) ጋራ ላይ ሆቴል እስከ 10፡00 ድረስ ሪፖርት በማድረግ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።
በቀጣይ ከሀገር ውጪ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ጥሪ የፊፋ ኢንተርናሽናል ውድድር መስኮት መመርያን በጠበቀ መልኩ ጥሪ የሚደረግላቸው ይሆናል።