ሽረ ምድረ ገነት ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

ሽረ ምድረ ገነት ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

ጋናዊው ግብ ጠባቂ ሽረ ምድረ ገነትን ለመቀላቀል ተስማምቷል።

በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐየ የሚመሩት እና በዝውውር መስኮቱ በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርመው የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በማከናወን ላይ የሚገኙት  ሽረ ምድረ ገነቶች አሁን ደግሞ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል፤ ክለቡን ለመቀላቀል የተስማማው ተጫዋች ደግሞ ጋናዊው ሬችሞንድ አዪ ነው።

የእግር ኳስ ሕይወቱ በሀገሩ ክለብ ቴቺማን ሲቲ ጀምሮ ባለፉት ዓመታት በ ‘West  African Football Academy (WAFA)’ ፣ ኸርትስ ኦፍ ኦክ እንዲሁም ድሪምስ መጫወት የቻለው የቀድሞ የጋና ወጣት ብሔራዊ ቡድን አባል አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ለሽረ ምድረ ገነት ፊርማውን ለማኖር ከስምምነት ደርሷል። ተጫዋቹ በትናንትናው ዕለት  አዲስ አበባ የገባ ሲሆን የሕክምና ምርመራውን ካጠናቀቀ በኋላም በይፋ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።