መቐለ 70 እንደርታዎች የነባሮችን ውል አራዝመዋል

መቐለ 70 እንደርታዎች የነባሮችን ውል አራዝመዋል

ምዓም አናብስት የአምስት ወጣት ተጫዋቾች ውል አራዝመዋል።

አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም እንዲሁም የነባሮችን ውል በማደስ በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የቆዩት እና ቀደም ብለው ዮሐንስ ዓፈራ እና ሐድሽ በርኸ ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት በአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት የሚመሩት መቐለ 70 እንደርታዎች አሁን ደግሞ የአምስት ወጣት ተጫዋቾችን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።

የቀኝ መስመር ተከላካዩ አማኑኤል ልዑል፣ አጥቂው ዓወት ኪዳነ፣ አማካዩ አዲሱ አድሐኖም፣ ግብ ጠባቂው ብስራት ገብረስላሴ እንዲሁም አማካዩ ቢንያም ተስፋይ ደግሞ በክለቡ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ከስምምነት የደረሱ ተጫዋቾች ናቸው።