የጦሩ የግብ ዘብ በአህጉራዊው መድረክ ሀገሩን እንዲወክል ጥሪ ደርሶበታል

የጦሩ የግብ ዘብ በአህጉራዊው መድረክ ሀገሩን እንዲወክል ጥሪ ደርሶበታል

 

የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአፍሪካ ዋንጫ አንድ ተጫዋች ያሳትፋል።

ላለፉት ዓመታት የመቻልን ግብ በቋሚነት የጠበቀው
ዩጋንዳዊው አልዮንዜ ናፍያን ሀገሩን ወክሎ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ደርሶታል።

ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ዋንጫ እንዲሁም በዓለም ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች ላይ ሀገሩን ወክሎ የተጫወተው ግብ ጠባቂው ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተሳትፎ ከነበራቸው አንጋፋው ዴኒስ ኦንያንጎ እና ቻርለስ ሉክዋጎ ጋር ለቋሚነት የሚፎካከር ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቅሎ ዝግጅት ጀምሯል።

በአህጉራዊው ውድድር ለመሳተፍ መመረጡን አስመልክቶ “ውድድሩ በአፍሪካ ትልቁ ውድድር ነው፤ ሁሉም ተጫዋች የሚመኘው እና ትላልቅ ተጫዋቾች ያፈራ ነው” የሚል አስተያየት የሰጠው ግብ ጠባቂው በሲቢኢ ፕሪምየር ሊግ በመሳተፍ ላይ ከሚገኙ ተጫዋቾች ውስጥ በትልቁ አህጉራዊው ውድድር የሚሳተፍ ብቸኛው ተጫዋች ነው።