በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኙት አርባ ምንጭ ከተማዎች የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላልፈዋል
በሊጉ ባደረጓቸው አስር ጨዋታዎች 5 ነጥብ ብቻ በመሰብሰብ 19ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት አርባምንጭ ከተማዎች ዛሬ ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል። በዚህ መሰረት ክለቡ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በረከት ደሙ እንዲሁም የአሰልጣኞች ቡድን አባላት እንዲሰናበቱ ውሳኔ ማስተላለፉ ተረጋግጧል።

ረፋድ ላይ በተካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ከተጠቀሰውን ውሳኔ በተጨማሪ ክለቡን በጊዜያዊነት የሚመሩ የአሰልጣኝ ቡድን ለመሾች በእጩዎች ዙርያ የመከረው ቦርዱ ከሰዓታት በኋላ በሚቀጥለው ውይይቱ የክለቡን ጊዜያዊ አሰልጣኝ፣ የቴክኒክ ቡድንና አዳዲስ የቦርድ አባላትን ይፋ እንደሚያደርግ የአርባምንጭ ከተማ መንግስት ኮምኒኬሽን ባጋራው መረጃ ተመላክቷል።

