ምዓም አናብስት አዲስ አሰልጣኝ ሾሙ

ምዓም አናብስት አዲስ አሰልጣኝ ሾሙ

በዛሬው ዕለት ከአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ጋር በስምምነት የተለያዩት መቐለ 70 እንደርታዎች አዲስ አሰልጣኝ ቀጠሩ።

ረፋድ ላይ መቐለ 70 እንደርታዎች ከአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ለመለያየት እንደተቃረቡና ሂደቱ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ መግለጻችን ይታወሳል። በዚህ መሰረት ክለቡ አመሻሽ ላይ ከአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ጋር በስምምነት መለያየቱ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ይፋ ያደረገ ሲሆን የአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን ቦታ የሚተኩ አሰልጣኝም ታውቀዋል።

በውድድር ዓመቱ አራት ነጥቦች የሰበሰቡት ምዓም አናብስት ክለቡን የሚመራ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ሲንቀሳቀሱ ከቆዩ በኋላ በመጨረሻም አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ሾመዋል።
ክለቡን የተረከቡት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም
ከዚህ ቀደም ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ ሐረር ቢራ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አርባምንጭ ከተማ፣ ሀድያ ሆሳዕና፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ወላይታ ድቻ ፣ ወልዋሎ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት መቐለ 70 እንደርታን ማሰልጠናቸው የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ ዳግም ወደ ምዓም አናብስቱ ቤት ተመልሰዋል።