ፌዴሬሽኑ ዮሐንስ ሳሕሌን መርጧል

ፌዴሬሽኑ ዮሐንስ ሳሕሌን መርጧል

የወቅቱ የዐፄዎቹ አሠልጣኝ ዩሐንስ ሳሕሌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ በመሆን መሾማቸው ይፋ ሆነ።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መምረጡ ይፋ ሆኗል።

የወቅቱ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ታዳጊ እና ዋናው ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት ከመምራታቸው በተጨማሪ ፌዴሬሽኑን በቴክኒክ ዳይሬክተርነት ማገልገላቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኙ እየሰሩበት ከሚገኘው ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር ንግግር ካደረገ በኋላ የውል ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ አመላክቷል።