የሊጉ አንድ ጨዋታ ተራዝሟል

የሊጉ አንድ ጨዋታ ተራዝሟል

በቀጣይ ሳምንት የሚደረገው የሊጉ አንድ ጨዋታ መራዘሙ ታውቋል።

አስራ አምስተኛ ሳምንቱን አገባዶ ከቀጣይ ማክሰኞ ጀምሮ አስራ ስድስተኛው ሳምንት የሚጀምረው ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አንድ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ በተስተካካይ መርሐግብር እንዲካሄድ መወሰነኑ ታውቋል።

ማክሰኞ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዘጠኝ ሰዓት ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘው የፋሲል ከነማ እና የሀድያ ሆሳዕና ብቸኛ ጨዋታ ከበዓል ጋር ተያይዞ በቀረበ ግምገማ ለመራዘሙ ምክንያት እንደሆነ የታወቀ ሲሆን በዚሁ ዕለት አዳማ የሚካሄዱ ጨዋታዎች ግን እንደሚኖሩ ታውቋል።

የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ የፋሲል ከነማ እና የሀድያ ሆሳዕና ጨዋታ ወደ ፊት በተስተካካይ እንደሚካሄድ ገልፆል።