አንተነህ ተፈራ አዲስ ክለብ አግኝቷል

አንተነህ ተፈራ አዲስ ክለብ አግኝቷል

አንተነህ ተፈራ ሸገር ከተማን ለቆ ወደ ሌላ የሊጉ ክለብ ለማምራት ተስማማ

ላለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ ቆይታ ያደረገው አጥቂው አንተነህ ተፈራ ከክለቡ ጋር ቀሪ ውል እያለው በስምምነት ተለያይቶ ወደ ባህርዳር ከተማ ለማቅናት ከስምምነት ደርሷል። በክልል ክለቦች ሻምፒዮና በሻኪሶ ከተማ ባሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ ወደ ኢትዮጵያ ቡና በማምራት በቡናማዎቹ ቤት ሦስት ጥሩ የውድድር ዓመታት ያሳለፈው ተጫዋቹ እሁን ደግሞ ከሸገር ከተማ የወራት ቆይታ በኋላ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ውል ወደ ባህርዳር ከተማ ለማቅናት ከስምምነት ደርሷል።