አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ከባድ ቅጣት ተጥሎባቸዋል

አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ከባድ ቅጣት ተጥሎባቸዋል

“የአርባምንጭ መውረድ አልተረጋገጠም” ያሉት ዋና አሰልጣኝ ከአወዳዳሪው አካል ከባድ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ በፋሲል ከነማ 2ለ0 ተሸንፎ ከሊጉ መውረዱን ማረጋገጡ ይታወሳል።

ከዚህ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው የቡድኑ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳም “አርባምንጭ ወረደ አትበሉ ፤ አልተረጋገጠም ፣ ባለፈው ዓመትም ሦስት ቡድን ይወርዳል ተብሎ ማንም አልወረደም ስለዚህ እኛም ላንወርድ እንችላለን።” ማለታቸውን ተከትሎ “የፌዴሬሽኑን ስም እና ዝና ያጎደፈ ፤ የፌዴሬሽኑን እና የአክሲዮን ማኅበሩ አሠራር ላይ በሀሰት የተመሠረተ መረጃ” ስለመስጠታቸው ሪፖርት የቀረበባቸው ሲሆን የውድድር እና ስነስርዓት ኮሚቴ አሰልጣኙን ለስድስት (6) ወር እንዲታገዱ እና 10,000 ብር እንዲከፍሉ ወስኖባቸዋል።