በካፍ ውድድሮች የሚሳተፉ የሀገራችን ክለቦች በየትኛው ስታዲየም ይጫወታሉ?

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና ኢትዮጵያ ዋንጫን በማሸነፍ በአፍሪካ መድረክ የሚሳተፉት ሲዳማ ቡናና ወልዋሎ ዓ/ዩ ከቀናት በፊት ተጋጣሚዎቻቸውን ማወቃቸው ይታወሳል። በድልድሉም ሲዳማ ቡና ከ ቻዱ ኤግሎስ ጋር ወልዋሎ ደግሞ ከሱዳኑ አል ሂላል አል ሳሕል ጋር መደልደላቸው ሲታወስ በሜዳቸውን የሚጫወቱበት ስታድየም ግን እስካሁን ድረስ አልታወቀም።
ሶከር ኢትዮጵያ ባደረገችው ማጣራት ክለቦቹ ምንም እንኳን በመዲናችን አዲስ አበባ በአበበ ቢቂላ ስታድየም የመጫወት ፍላጎት ቢኖራቸውም ስታድየሙ ከካፍ በሚቀርበብት የማስተካከያ ሪፖርት አንፃር በሜዳው የመጫወት ዕድላቸው ጠባብ እንደሆነ ታውቋል። ይህንን ተከትሎም ጨዋታዎቹ በድሬዳዋ ስታድየም የመካሄድ ዕድላቸው ሰፊ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በጉዳያ ዙሪያ የሚፈጠሩ አዳዲስ ነገሮች ካሉም እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል።

