ኢትዮጵያ መድን ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማምቷል

ኢትዮጵያ መድን ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማምቷል

ወደ ዝውውሩ በመግባት ተጫዋቾችን ያስፈረሙት ኢትዮጵያ መድኖች ሁለት ተጫዋቾችን በድጋሚ ለማስፈረም ተስማምተዋል።

በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የሚመሩት ኢትዮጵያ መድኖች ለቀጣይ የውድድር ዘመን ቡድናቸውን ለማጠናከር ከደቂቃዎች በፊት አቡበከር ሻሚል እነ አሸናፊ ሀፍቱን ለማስፈረም በመስማማት ወደ ዝውውሩ የገቡ ሲሆን አሁን ደግሞ ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተቃርበዋል።

የመጀመርያው ተጫዋች አማካዩ  ከማል ሀጂ ነው። በከፍተኛ ሊጉ በስለጤ ወራቤ እና በሊጉ  ለሀድያ ሆሳዕና የተጫወተ ሲሆን በዘንድሮ ዓመት በከፍተኛ ሊግ ለደሴ ከተማ አንበል በመሆን በአብዛኛው ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ እና ሦስት ጎሎች በማስቆጠር ሰባት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማመቻቸት ጥሩ ዓመት ካሳለፈ በኋላ አሁን ለኢትዮጵያ መድን ለመጫወት ተስማምቷል።

ሁለተኛው የግራ መስመር ተከላካዩ ገለታ ኃይሌ ሲሆን ከዚህ ቀደም በጅማ አባ ጅፋር ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር  የቆይታ አድርጎ አሁን ለኢትዮጵያ መድን ለመጫወት ተስማምቷል።