ያለፈውን አንድ ዓመት ከኢትዮጵያ መድን ጋር ቆይታ የነበረው ጋናዊው ተከላካይ ውሉን ማራዘሙን አውቀናል።

ዛሬ ወደ ዝወውሩ የገቡት ኢትዮጵያ መድኖች አቡበከር ሻሚል፣ አሸናፊ ሀፍቱ፣ ገለታ ሀይሉ እና ከማል ሀጂን ለማስፈረም የተስማሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ጋናዊው ተከላካይ እስማኤል አብዱል ጋንዩ ለማቆየት መስማማታቸውን አውቀናል።
ወደ ሀገራችን ከመምጣቱ በፊት ቲ ፒ ማዜምቤ ፣ አሻንቲ ኮቶኮ ፣ ካሬላ ዩናይትድ የተጫወተ ሲሆን ወደ ድሬደዋ ከተማ በመምጣት ካሳለፈ በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከኢትዮጵያ መድን ቆይታ ያደረገው። ከመድኖች ጋር ያለው ውል የተጠናቀቀው ተከላካዩ በሌሎች የሀገር ውስጥ ክለቦች ሲፈለግ ቢቆይም እርሱ ግን በኢትዮጵያ መድን ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ውሉን ማራዘሙን ሰምተናል።

