👉 “ውሳኔው ተገቢ አይደለም ይግባኝ እንጠይቃለን።” የአርባምንጭ ከተማ ቡድን መሪ

👉 “ውሳኔው ተገቢ አይደለም ይግባኝ እንጠይቃለን።” የአርባምንጭ ከተማ ቡድን መሪ

የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ላይ የተወሰነውን ውሳኔ ተገቢ አይደለም ሲሉ  የአርባምንጭ ከተማ ቡድን መሪ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ በፋሲል ከነማ 2ለ0 ተሸንፎ ከሊጉ መውረዱን ካረጋገጠበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የቡድኑ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ “አርባምንጭ ወረደ አትበሉ ፤ አልተረጋገጠም ፣ ባለፈው ዓመትም አራት ቡድን ይወርዳል ተብሎ ማንም አልወረደም ስለዚህ እኛም ላንወርድ እንችላለን።” በማለት በሰጡት አስተያየት  የእግርኳሱን የበላይነት የሚመሩት አካሎች አሰራር ላይ በሐሰት መረጃ ሰጥተዋል በሚል ትናንት የስድስት (6) ወር ዕገዳ እና 10ሺህ ብር እንዲከፍሉ ቅጣት ተወስኖባቸዋል።

ውሳኔውን ተከትሎ ያናገርናቸው የአርባምንጭ ከተማ ቡድን መሪ አቶ ፀጋዬ ገሌ “ውሳኔው ረፋድ አምስት ሰዓት ላይ ነው የደረሰን። ውሳኔው ተገቢ አይደለም ይግባኝ እንጠይቃለን።
አሁን ከሚመለከታቸው የክለቡ የበላይ አመራሮች ጋር እስከ ምን ድረስ መሄድ እንዳለብን ተነጋግረን ከፊታችን ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ ይግባኝ እንጠይቃለን። ወደ የእግርኳሱ ገላጋይ ፍርድ ቤት (ካስ) ድረስ እንሄዳለን።” ብለውናል

( ይህ ንግግር የተደረገው በትናንትናው ዕለት መሆኑን ለማስታወቅ እንወዳለን )