ቢኒያም በላይ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ተቃርቧል

ቢኒያም በላይ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ተቃርቧል

የ2015 የዓመቱ የሊጉ ኮከብ ተጫዋች እና የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ቢኒያም በላይ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ መቃረቡ ተሰምቷል።

ቢኒያም በላይ አሳዳጊ ክለቡን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ በአልባኒያው ክለብ ከስከንደርቡ ጋር የሁለት ዓመታት ስኬታማ ቆይታ ካደረገ በኋላ በመቀጠል በስዊድኖቹ ክለቦች ስሪያንስካ እና ኡመያ በመጫወት ነበር ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ለሲዳማ ቡና ፣ ለመቻል እንዲሁም ለቅዱስ ጊዮርጊስ በተለይም በዋንጫ የታጀበ ስኬታማ ቆይታ ከማድረጉ ባሻገር የ2015 የሊጉ ኮከብ ተጫዋች መሆኑ ይታወሳል። ያለፉትን ሁለት ዓመታትም ለሀዋሳ ከነማ ግልጋሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

ከሐይቆቹ ጋር የነበረው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቢቆይም በኋላም ማረፊያው የቀድሞ ክለቡ ሲዳማ ቡና ሊሆን መቃረቡን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች። ቢኒያም በቻምፒዮኖቹ ቤት ለሁለት ዓመታት ለመጫወት ይስማማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።