ፍፁም ጥላሁን ቀጣይ ማረፊያው የት ይሆን?

ፍፁም ጥላሁን ቀጣይ ማረፊያው የት ይሆን?

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እንደማይቀጥል ዕርግጥ የሆነው ፍፁም ጥላሁን ወደ ሌላ ክለብ ለማቅናት ተቃርቧል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያሳለፈው እና ስምንት ጎሎች በማስቆጠር እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጭምር ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው አጥቂው ፍፁም ጥላሁን ከፈረሰኞቹ ጋር የውል ዘመኑ መጠናቀቁን ተከትሎ በአንዳንድ ነገሮች  መስማማት ባለመቻሉ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ከሁለት ዓመት በኋላ መለያየቱን ተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጦልናል።

የእግር ኳስ ጉዞውን በቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊዎች የጀመረው እና በኢትዮጵያ ቡና ከ20 ዓመት በታች እንዲሁም በዋናው ቡድን ውስጥ ተጫውቶ እራሱን ማሳደግ የቻለው ፍፁም፤ በመቀጠልም ለአዲስ አበባ ከተማ እና ለባህር ዳር ከተማ እንዲሁም በቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ዓመት የቆየ ሲሆን ቀጣይ ማረፊያውን በቅርቡ የሚያሳውቅ ይሆናል።