የሊጉን ቻምፒዮንነት ክብር ከሲዳማ ቡና ጋር የተቀዳጀው አማካዩ ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል።

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሬድዋን ናስር ሀዋሳ ከተማን በይፋ ተቀላቅሏል። በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመሩት ሐይቆቹ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ስብስባቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን ቀደም ሲል ቃልኪዳን ዘላለም፣ ብሩክ በየነ፣ ሙሴ ከበላ እና ቃለአብ ውብሸትን ወደ ስብስባቸው በመቀላቀል እንዲሁም የብሩክ ታደለ እና የግብ ጠባቂው ምንተስኖት ጊንቦን ውል በማራዘም ዝውውር የጀመሩት ሀይቆቹ አሁን ደግሞ የሬድዋን ናስርን ዝውውር በማጠናቀቅ የቡድናቸውን ጥልቀት አሳድገዋል።
ሬድዋን የእግር ኳስ ህይወቱን ከአዲስ አበባ ከተማ ከ20 ዓመት በታች ቡድን በመጀመር እስከ ዋናው ቡድን መድረስ የቻለ ተጫዋች ነው። በመቀጠል በኢትዮጵያ ቡና ከወንድሙ አቡበከር ናስር ጋር በጥምረት መጫወት ችሏል። ላለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ በሲዳማ ቡና የነበረውን ቆይታ በሻምፒዮንነት አጠናቆ አሁን አዲስ ፈተናን ለመጋፈጥ የሀዋሳ ከተማን ስብስብ ተቀላቅሏል።

